ሊቀመንበራችን በወልድያ ሊገነባ ለታቀደው ስታዲዮም የሚያስፈልገውን 200 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ወጪ ለመሸፈን ቃል ገቡ
|
የወልዲያ ስታድየም የወጣቶች ማዕከል ፕሮጀክት በዋነኛነት 25,000 ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ስታድየምን የያዘና በተዛማጅም ቤተመጻሕፍት፣ የወጣቶች ማዕከል፣ ዘመናዊ የመዋኛ ሥፍራ፣ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴል፣ ጂምናዝየም፣ ሱቆችና የአስተዳደር አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ያካተተ ነው፡፡ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በክብር እንግድነት በተገኙበት በዚህ ፕሮግራም ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሣ ተክለብርሃንን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የመንግሥት ባለሥልጣኖች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና በልማት አጋርነታቸው ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ ከፍተኛ |
![]() |
|
የቅድመ-ቴሎቶኑ ፕሮግራም ዓላማ የስታድየሙን ፕሮጀክት በማስተዋወቅና አጠቃላይ እቅዱን ይፋ በማድረግ ወደፊት ለሚካሔደው ዋናው ቴሌቶን ድጋፍ ሰጪ አካላትን በመገናኘት ለስታድየሙ ግንባታ እርሾ የሚሆን ገቢ ለማሰባሰብ እንደሆነ በአዲስ አበባው ኮሚቴ የቦርድ ሰብሳቢ በዶ/ር አረጋ ይርዳው በዝርዝር ተገልጿል፡፡ በዚሁ መሠረት የስታድየሙ ፕሮጀክት ዝርዝር እቅድ የቀረበ ሲሆን በአካባቢው ሊገነቡ የተወጠኑት ቤተ መጻሕፍት፣ የባህል ማዕከል፣ የመዋኛ ሥፍራና የእንግዶች መስተናገጃን ጨምሮ በርካታ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ከነወጪ ግምታቸው ለተሳታፊዎች ግንዛቤ ቀርበዋል፡፡ በሀገራችን የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚናን በመጫወት ላይ የሚገኙት ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ኩባንያዎቻቸውን በማስተባበር በቀረበው የግንባታ ፕሮጀክት ዋናውን ሥፍራ የሚይዘውንና 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ/ ተመልካቾችን የሚያስተናግደውን ዘመናዊስታድየም በታቀደለት የ200 ሚሊዮን ብር የወጪ ግምት ለማስገንባት ቃል ገብተዋል፡፡ |
|
