«ፈገግታ
የሌለው ንግድ
ቤት አይከፈት»
ይላሉ ቻይናዎች፤
በእኛም ሀገር
«ከፍትፍቱ ፊቱ»
የሚል አባባልም
አለ፡፡ ይህ
አባባል ተጨባጭ
ዕውነታን መሠረት
ያደረገ መሆኑን
በዕለታዊ የሥራና
የማኅበራዊ
እንቅስቃሴያችን
የምንገነዘበው
ነው፡፡ በመሆኑም
ደንበኞችን
በመበዝበዝና
በማንገላታት
ሳይሆን በጥሩ
ትህትናና በመልካም
አቀባበል ቀልጣፋ
አገልግሎት
መስጠትን ዋናው
የሥራ መመሪያችን
አድርገን በመተግበር
ላይ እንገኛለን፡፡
ያለፉት ሦስት
ዓመታት የሥራ
ተሞክሮ እንደሚያሳየው
ለደንበኛ ክብርን
የሰጠ አያያዛችን
ውጤትን አስገኝቶልናል፡፡
ለኩባንያዎቻችን
ዕድገት፣ መስፋፋትና
ቀጣይነት ደንበኞች
አስተማማኝ
ዋስትና መሆናቸውን
በሚገባ እናውቃለን፡፡
ስለዚህ ደንበኞች-ተኮር
(Customer-Focused) የአሠራር
መንገድን በመከተል
ለሽያጭ የምናቀርበው
ምርትና አገልግሎት
ለደንበኞች
እርካታን (Satisfaction) መስጠቱንና
አለመስጠቱን
በመከታተል
እርካታን እንደመለኪያ
(Yardstick) አድርገን
መከተል መመሪያችን
አድርገን ይዘናል፡፡
ዐቢይ ትኩረታችን
የደንበኞችን
ፍላጎት ማርካት
በመሆኑ የምንሸጠው
«እርካታን»
ነው የሚል
እምነት አለን፡፡
ለደንበኞቻችን
ያለንን ክብር
ለመግለጽ፣
የኩባንያዎቻችን
ሠራተኞች ከደንበኞች
ጋር እንዲተዋወቁና
ልምድ እንዲለዋወጡ
ለማስቻል በየዓመቱ
የ«ደንበኞች
ቀን» ማክበር
ባህላችን አድርገነዋል፡፡
በዘንድሮው
የ«ደንበኞች
ቀን» በዓል
ላይ በርካታ
ደንበኞቻችን
ተሳትፈዋል፡፡
ለዕድገትና
ለሕልውናችን
ያላቸውን ጉልህ
አስተዋጽዖ
ለማስገንዘብ
ለሀገር ውስጥና
ለውጭ ሀገር
ምርት ደንበኞቻችን
የዋንጫና የሠርቲፊኬት
ሽልማት አበርክተናል፡፡
ይህም በዓል
የታሰበለትን
ግብ የመታና
ውጤታማ ነበር፡፡
በዓሉ የተሳካ
እንዲሆን ጥረት
ላደረጉት የኩባንያዎቹ
ሠራተኞች፤
እንዲሁም ከሀገር
ውስጥና ከውጭ
ሀገር ጥሪያችንን
አክብራችሁ
ለተሳተፋችሁት
ደንበኞቻችን
ከፍተኛ ምሥጋናዬን
አቀርባለሁ፡፡
የ«ደንበኞች
ቀን» ማክበር
ያለው ጠቀሜታ
ከፍተኛ በመሆኑም
ዕለቱን በየዓመቱ
በተጠናከረ
ሁኔታ ማክበሩን
የምንገፋበት
ይሆናል፡፡