እንኳን
ከዘመነ-ማቴዎስ
ወደ
ዘመነ-ማርቆስ
በሰላም
አሸጋገራችሁ!
ሊቀመንበራችን ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ለመላው የድርጅቶቻችንን ሠራተኞችና ቤተሰቦች አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ያስተላለፉትን መልዕክት ስገልጽ ከፍተኛ ደስታ እየተሰማኝ ነው፡፡
ለሀገራቸውና
ለወገናቸው
አለኝታ
የሆኑት
ሊቀመንበራችን
እንዳለፉት
ዓመታት
ዘንድሮም
በተለመደው
ልግስናቸው
የልዩ
ችሮታ
የአዲስ
ዓመት
በዓል
የ«እንኳን
አደረሳችሁ»
የአንድ
ወር
ደመወዝ
ክፍያ
በመፍቀዳቸው
በሲ.ሲ.ኦ
ቢሮና
በሥሩ
የተደራጁት
11
ኩባንያዎች
ውስጥ
ያሉ
ሠራተኞች
ተጠቃሚ
እንዲሆኑ
ተደርጓል፡፡
ቅንነትና
ደግነትን
የተላበሱት
ሊቀመንበራችንና
ቤተሰቦቻቸው
ለዘመን
መለወጫ
በዓል
መዋያ
ልዩ
ስጦታ
በማበርከታቸው
የተሰማኝን
አድናቆት
በመላ
ሠራተኞች
ስም
በአክብሮት
እገልፃለሁ፡፡
በአዲሱ
ዓመት
መግቢያ
ላይ
ሆነን
ያለፈው
ዓመት
የሥራ
ሂደትና
እንቅስቃሴያችንን
ስንመለከት
አበረታችና
በጎ
ጅምሮች
የታዩበት
ሆነው
እናገኛለን፡፡
በአሁኑ
ጊዜ
በድርጅቶቻችን
ውስጥ
በተቀናጀ
አመራር
ስልት
እየተመዘገበ
ያለው
ውጤት
ለበለጠ
ሥራ
የሚያተጋ
ነው፡፡
ለዚህ
የስኬት
ደረጃ
ለመድረስ
መላው
ሠራተኛና
አመራር
ያበረከተው
አስተዋጽዖ
ደምቆ
የሚታይ
ሆኗል፡፡
በዘንድሮውም
አዲስ
ዓመት፣
በአዲስ
መንፈስና
በአዲስ
ጉልበት
በመንቀሳቀስ
ውጥን
ሥራዎቻችንን
ለፍሬ
ለማብቃት፤
የጀመርነውን
ኩባንያዎቻችንን
የማጠናከርና
የማስፋፋት
እንቅስቃሴ
ከዳር
ለማድረስ
እጅ
ለእጅ
ተያይዘን
በሕብረትና
በመተሳሰብ
እንድንሠራ
ጥሪዬን
አስተላልፋለሁ፡፡
ቸሩ
ፈጣሪያችን
ለሊቀመንበራችን
ለሼክ ሙሐመድ
ሁሴን አሊ
አል-አሙዲ፣
ለወንድሞቻቸውና
ለመላው ቤተሰባቸው፣
ለድርጅቶቻችን
ሠራተኞችና
መላው ቤተሰባቸው፣
በአጠቃላይም
ለሀገራችን
ሕዝብ ሰላም፣
ጤናና ብልጽግና
እንዲሰጥልን
ልባዊ ምኞቴን
እገልጻለሁ፡፡
መልካም አዲስ
ዓመት!