በሄልሲንኪ
ሲካሄድ በሰነበተው
10ኛው
የዓለም
አትሌቲክስ ሻምፒዮን
የተሳተፈው የኢትዮጵያ
አትሌቲክስ ቡድን
ደማቅ የጀግና አቀባበል
እንዲደረግለት ሊቀመንበራችን
ሼክ ሙሐመድ ሁሴን
አሊ አል-አሙዲ የተለመደውን
በጎ ተግባር አከናውነዋል፡፡
የአትሌቲክስ ቡድናችን
በሊቀመንበራችን
በጎ ፍቃድ አንድ ነጥብ
ሁለት ሚሊዮን ብር
ወጪ ልዩ ቻርተር አውሮፕላን
ተመድቦለት ወደ ሀገሩ
በክብር ተመልሷል፡፡
ቡድኑ ቦሌ አውሮፕላን
ጣቢያ እንደደረሰም
ዶ/ር አረጋ ይርዳው
የሚድሮክ ኢትዮጵያ
ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ
ኦፊሰርና አቶ ተክሉ
ኃይሌ የሚድሮክ ኢትዮጵያ
የትሬዠሪ፣ ፋይናንስና
አካውንቲንግ ማኔጀር፤
ጉዳዩ ከሚመለከታቸው
የመንግሥት ባለሥልጣናት
ጋር በመሆን የክብር
አቀባበል አድርገውለታል፡፡
በሄልሲንኪው ሻምፒዮና
ዘጠኝ ሜዳሊያዎች
በማግኘት ኢትዮጵያ
ከዓለም ሦስተኛ ደረጃ
እንድትይዝ ላበቃው
ለዚሁ ቡድን በሼክ
ሙሐመድ
ልዩ ፍቃድ ደረጃቸውን
የጠበቁ አስር ዘመናዊ
ማርቼዲሶች ከቦሌ
አውሮፕላን ማረፊያ
እስከ አዲስ አበባ
እስታዲየም በክብር
አጅበው እንዲያጓጉዟቸው
በማድረግ የአቀባበል
ሥነ-ሥርዓቱ ደማቅ
እንዲሆን የጎላ አስተዋጽዖ
አበርክተዋል፡፡
በሌላ
በኩል ሊቀመንበራችንና
የሚድሮክ ኢትዮጵያ
ባለቤት ሼክ ሙሐመድ
ሁሴን አሊ አል-አሙዲ
በተለመደው ችሮታቸው
ለኢትዮጵያ ወጣቶች
የልማትና የሰላም
ማህበር ማጠናከሪያ
የሚውል የሁለት ሚሊዮን
ብር እርዳታ ለገሱ፡፡
የማህበሩ ማደራጃ
በዓል በቅርቡ በሸራተን
አዲስ በተካሄደበት
ወቅት ሊቀመንበራችን
ባደረጉት ንግግር፤
ወጣቱ ትውልድ ለሀገሪቱ
ዋነኛ ሀብት እንደመሆኑ
መጠን የሁሉም ሕብረተሰብ
ክፍል ድጋፍና እገዛ
እንደሚያስፈልገው
አስገንዝበዋል፡፡
ወጣቶችም ሀገርን
ለማበልፀግ ያለባቸውን
ኃላፊነት ለመወጣት
በከፍተኛ ደረጃ መንቀሳቀስ
እንዳለባቸው በአጽንኦት
ገልፀዋል፡፡ በዚህም
በዓል ላይ አፈ-ጉባዔ
ዳዊት ዮሐንስን ጨምሮ
መንግስታዊና መንግስታዊ
ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች
ተሳታፊ ሆነዋል፡፡