በሚድሮክ
ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግል
ኩባንያ የለገደምቢ
የወርቅ ፍለጋ ፈቃድና
ፕሮግራም አካል የሆነው
የምሥራቅ ሳካሮ ፕሮጀክት
ከቅድመ ምርት ጥናት
ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ
የተሸጋገረበት ሒደት
በይፋ ተመርቆ ተከፈተ፡፡
በይፋ የተመረቀው
ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን
2000 ዓ.ም ..እ.ኤ.አ. ኦገስት
2 ቀን 2008 ዓ.ም.. በሚድሮክ
ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ
ኦፊሰርና የሚድሮክ
ወርቅ ማዕድን ኩባንያ
ዋና ሥራ አስኪያጅ
በዶ/ር አረጋ ይርዳውና
በአዶ ሻኪሶ ወረዳ
አስተዳደሪ በአቶ
ተስፋዬ ዋዩ ሲሆን
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት
ላይ የሳካሮ አካባቢ
የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና
የሀገር ሽማግሌዎች
የኩባንያው የዋናው
መሥሪያ ቤትና የለገደምቢ
ማኔጅመንት የሥራ
ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው
እንግዶችና ሠራተኞች
ተገኝተዋል፡፡
የሳካሮ
ፕሮጀክት ከለገደምቢ
የወርቅ ማምረቻ ሥፍራ
5 ኪ.ሚ ርቀት ላይ 10 ስኮየር
ኪሎ ሜትር በሚሸፍን
ሥፍራ ላይ የሚካሄድ
ሲሆን በለገደምቢ
የመሬት ውስጥ የወርቅ
ፍለጋ የተገኘውን
ዕውቀት በማዳበር
የመሬት ውስጥ ለውስጥ
(Undergraund) የወርቅ ፍለጋ
የሚካሄድበት ከመሆኑም
በላይ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ
የማምረት ደረጃ ላይ
የሚደርስ ፕሮጀክት
ነው፡፡ ኩባንያው
ያካበተውን የወርቅ
ማምረት ዕውቀትና
የሚጠቀምባቸውን
መሣሪያዎች የበለጠ
በማሻሻል የ..ሚድሮክ
ወርቅ ራዕይ 2020ን እውን
ለማድረግ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ የሚኖረው
ፕሮጀክት እንደሆነ
ዶ/ር አረጋ ይርዳው
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት
ላይ ባደረጉት ንግግር
አስታውቀዋል፡፡
ለብዙ
ዓመታት ልጆቻችን
ሳይቀሩ ሊሰሩበት
የሚችሉ እድሜው የተራዘመ
ኩባንያ ሊኖረን መቻሉን
የገለፁት ዶ/ር አረጋ
ይህ ሊሆን የቻለው
ኩባንያው እያመረተ
የሚያገኘውን ገቢ
ለአካባቢው ልማትና
የማምረት ሂደቱን
ለማስፋፋት ተግባር
እንዲያውለው ባለሀብቱ
ሼክ ሙሐመድ ሁሴን
አሊ-አልአሙዲ በመፍቀዳቸውና
ልዩ እገዛ በማድረጋቸው
ሲሆን ባለፉት 3 ዓመታት
በተደረገው ጥናትም
ከለገደምቢ ቀጥሎ
2ኛ ቤታችን የሆነውን
የሳካሮን አልፈን
ወደ ዋርሲቲ ጭምር
የምንዘልቅበትን
መሠረት ጥለናል ብለዋል፡፡
በሳካሮ የመሬት ውስጥ
ለውስጥ የወርቅ ፍለጋ
ፕሮጀክት መግቢያና
መውጫ ሥፍራ ላይ በተከናወነው
ሥነ-ሥርዓት ተካፋይ
የሆኑ የኦዶ ሻኪሶ
ወረዳ አስተዳደሪ
አቶ ተስፋዬ ዋዩ በበኩላቸው
ባደረጉት ንግግር
ልማቱ የክልላችን
ሲሆን የአካባቢው
ሕዝብ የልማቱ ቀጥተኛ
ተጠቃሚ መሆኑን አውቆ
ለኩባንያው ጥረቶች
ማናቸውንም ትብብር
ማድረግ ይጠበቅበታል
ካሉ በኋላ የወረዳው
አስተዳደር ከሚድሮክ
ወርቅ ማዕድን ኩባንያ
ጎን በመሰለፍ ማናቸውንም
ትብብር እንደሚያደርግ
አረጋግጠዋል፡፡
በሌላ
በኩል ደግሞ የሚድሮክ
ወርቅ ማዕድን ኩባንያ
ማኔጅመንትና መሠረታዊ
የሠራተኛ ማሕበር
በመሀከላቸው ፀንቶ
የቆየውንና ጊዜው
የተጠናቀቀውን የሕብረት
ስምምነት በወቅቱ
በማደስ በየተወካዮቻቸው
አማካኝነት የሕብረት
ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት
አካሂደዋል፡፡ ለሦስት
ዓመታት በሥራ ላይ
የሚቆየው አዲሱ የሕብረት
ስምምነት የሠራተኛውን
መብትና ጥቅማ ጥቅሞች
የሚያዳብሩ ተጨማሪ
የማሻሻያ ሐሳቦች
የታቀፉበት ሲሆን
እንደተለመደው ማኔጅመንቱ
የሠራተኞችን ጥያቄ
ለመመለስ በአጋርነት
መሰለፉን አረጋግጦበታል፡፡የሕብረት
ስምምነቱን የተፈራረሙት
የኩባንያው ዋና ሥራ
አስኪያጅ ዶ/ር አረጋ
ይርዳውና የሠራተኛ
ማሕበሩ ሊቀመንበር
አቶ ገዛኸኝ ገ/ዮሐንስ
ሲሆኑ በሥነ- ሥርዓቱ
ላይ አቶ ገዛኸኝ ባደረጉት
ንግግር የሕብረት
ስምነቱ ከቀድሞው
የተሻለ የሠራተኛውን
ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ
የመለሰ መሆኑን በመግለፅ
ዶ/ር አረጋ ይርዳው
ነፃ ግልፅና በተናገሩት
የሚፀኑ እውነተኛ
መሪ መሆናቸውን ጠቅሰው
ለስምምነት ፊርማው
መሳካት ላበረከቱት
ልዩ አስተዋፅኦ ከፍተኛ
ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ዶ/ር
አረጋ ይርዳው በአካባቢው
የተገኙበትን አጋጣሚ
በመጠቀም ከተለያዩ
የሥራ ኃላፊዎች ጋር
ውይይት በማድረግ
የሥራ መመሪያ ከመስጠታቸውም
በላይ በኦዶ ሻኪሶ
2ኛ ደረጃና መሰናዶ
ት/ቤት በመገኘት በኮርፓሬት
ደረጃ ለት/ቤቱ የተበረከቱትን
ልዩ ልዩ ሥጦታዎችን
ተመልክተዋል፡፡